1 ዜና መዋዕል 27:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስተዋይና ጸሓፊ የነበረው በአባቱ በኩል የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የአክማኔም ልጅ ኢያሔኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ የሆነው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪና ጸሓፊ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ደግሞ የንጉሡ ልጆች ሞግዚት ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል የንጉሡን ልጆች ያገለግል ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ዳዊት አጐት የሆነው ዮናታን ብልኅ አማካሪና የታወቀ ምሁር ነበር፤ እርሱና የሐክሞኒ ልጅ ይሒኤል የንጉሡ ልጆች አስተማሪዎች ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስተዋይና ጸሐፊ የነበረው የዳዊት አጎት ዮናታን አማካሪ ነበረ፤ የሐክሞኒም ልጅ ይሒኤል ከንጉሡ ልጆች ጋር ነበረ፤ |
የዳዊትም ኀያላን ቍጥር ይህ ነበረ፤ የሠላሳው አለቃ የአኪማን ልጅ ኢያቡስቴ ነበረ፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰው በአንድ ጊዜ ገደለ።