የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይፉንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ በአንድ ጊዜ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀረውንም ሕዝብ ለወንድሙ ለአቢሳ ሰጠው፤ እነርሱም በአሞን ልጆች ላይ ተሰለፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩትም ሰዎች በወንድሙ በአቢሳ ሥር ሆነው አሞናውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀረውንም ሕዝብ ለወንድሙ ለአቢሳ ሰጠው፤ እነርሱም በአሞንም ልጆች ላይ ተሰለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠራዊቱ ቀሪውን ክፍል በወንድሙ በአቢሳ ትእዛዝ ሥር አደረገ፤ አቢሳም እነርሱን በዐሞናውያን ፊት ለፊት አሰለፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀረውንም ሕዝብ ለወንድሙ ለአቢሳ ሰጠው፤ በአሞንም ልጆች ላይ ተሰለፉ። |
የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይፉንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ በአንድ ጊዜ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።
ኢዮአብም በፊቱና በኋላው ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ጐልማሶችን መረጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጋር ተዋጉ።