Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 11:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም አቢሳ የሦ​ስቱ አለቃ ነበረ፤ ሰይ​ፉ​ንም በሦ​ስት መቶ ላይ አን​ሥቶ በአ​ንድ ጊዜ ገደ​ላ​ቸው፤ በሦ​ስ​ቱም መካ​ከል ስሙ የተ​ጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ። እርሱም ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎች ገደለ፤ ከዚህም የተነሣ እንደ ሦስቱ ሁሉ ዝነኛ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፥ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 የኢዮአብ ወንድም አቢሳ የሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች የበላይ አለቃ ነበር፤ እርሱ ጦሩን አንሥቶ ሦስት መቶ ሰዎችን ገድሎ ስለ ነበር እንደ ሦስቱ ዝነኞች ወታደሮች ታዋቂ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የኢዮአብም ወንድም አቢሳ የሦስቱ አለቃ ነበረ፤ ጦሩንም በሦስት መቶ ላይ አንሥቶ ገደላቸው፤ በሦስቱም መካከል ስሙ የተጠራ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 11:20
10 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ከኢ​ዮ​አብ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከኢ​ዮ​አ​ብም ወን​ድም ከሶ​ር​ህያ ልጅ ከአ​ቢሳ እጅ በታች ሢሶ​ውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶ​ውን ላከ። ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእ​ና​ንተ ጋር እወ​ጣ​ለሁ” አላ​ቸው።


በዚ​ያም ሦስቱ የሦ​ር​ህያ ልጆች ኢዮ​አ​ብና አቢሳ፥ አሣ​ሄ​ልም ነበሩ፤ የአ​ሣ​ሄ​ልም እግ​ሮቹ ፈጣ​ኖች ነበሩ፤ እንደ ዱር ሚዳ​ቋም ሯጭ ነበረ።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “አሁን አቤ​ሴ​ሎም ከአ​ደ​ረ​ገ​ብን ይልቅ የከፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ብን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አግ​ኝቶ ከዐ​ይ​ና​ችን እን​ዳ​ይ​ሰ​ወር፥ አንተ የጌ​ታ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ወስ​ደህ አሳ​ድ​ደው” አለው።


የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።


ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


“ይህን አደ​ርግ ዘንድ አም​ላኬ ሆይ፥ ለእኔ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም ለሞት አሳ​ል​ፈው አም​ጥ​ተ​ው​ታ​ልና የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ደም እጠ​ጣ​ለ​ሁን?” አለ። ስለ​ዚ​ህም ዳዊት ይጠ​ጣው ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም። ሦስ​ቱም ኀያ​ላን ያደ​ረ​ጉት ይህ ነው።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ተራ በሆ​ኑት በሦ​ስቱ መካ​ከል የከ​በረ ነበረ፥ አለ​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ነገር ግን ወደ ፊተ​ኞቹ ወደ ሦስቱ አል​ደ​ረ​ሰም።


እኅ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ሶር​ህ​ያና አቢ​ግያ ነበሩ። የሶ​ር​ህ​ያም ልጆች አቢሳ፥ ኢዮ​አብ፥ አሣ​ሄል እኒህ ሦስቱ ነበሩ።


ዳዊ​ትም ኬጤ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክ​ንና የሶ​ር​ህ​ያን ልጅ የኢ​ዮ​አ​ብን ወን​ድም አቢ​ሳን፥ “ወደ ሳኦል ወደ ሰፈሩ ከእኔ ጋር የሚ​ገባ ማን ነው?” ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፤ አቢ​ሳም፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር እገ​ባ​ለሁ” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos