1 ዜና መዋዕል 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም በፊቱና በኋላው ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ጐልማሶችን መረጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም ከፊቱና ከኋላው ጦር መኖሩን አየ፤ ስለዚህ በእስራኤል የታወቁትን ጀግኖች መርጦ ሶርያውያንን እንዲገጥሙ አሰለፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም ውግያው በፊትና በኋላ እንደሚደረግ ባየ ጊዜ ከእስራኤል ምርጥ ምርጦችን ሁሉ ለይቶ በሶርያውያን ላይ አሰለፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ የጠላት ሠራዊት ከፊትና ከኋላ በኩል አደጋ እንደሚጥልበት ተመለከተ፤ ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ጀግኖች የሆኑትን መርጦ በሶርያውያን ሠራዊት ፊት ለፊት አቆማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም በፊትና በኋላ ሰልፍ እንደ ከበበው ባየ ጊዜ ከእስራኤል ምርጥ ምርጦችን ሁሉ ለይቶ በሶርያውያን ላይ አሰለፋቸው። |
እነዚያም ከከተማ ወጥተው ተቀበሉአቸው፤ በእስራኤል ልጆች ሠራዊት መካከልም አገቡአቸው፤ እኒያ ከወዲያ፥ እኒህም ከወዲህ ሆነው አንድ እንኳን ሳይቀርና ሳያመልጥ ገደሉአቸው።