መዝሙር 85:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤ ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝብህን በደል አስቀረህ፥ ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን ከመቈጣት ታገሥህ፤ ብርቱ ቊጣህንም መለስህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኻለሁና ይቅር በለኝ። |
ስለዚህ በመቅሠፍቱ እንዳያጠፋቸው ይመለስ ዘንድ፣ እርሱ የመረጠው ሙሴ በመካከል ገብቶ፣ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፣ እንደሚያጠፋቸው ተናግሮ ነበር።
በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤ ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።
በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አንዳችም አይገኝም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤ ከቶም የለም፤ እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ቅሬታዎች እምራለሁና።
ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፣ በደልሽ ትዝ ሲልሽ ታፍሪያለሽ፤ ከውርደትሽም የተነሣ አፍሽን ከቶ አትከፍቺም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”
እግዚአብሔር ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤