መዝሙር 63:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሴን ለማጥፋት የሚሹ ግን፣ ወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴ ከኋላህ ተቆራኘች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ሁሉ ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ ፈራ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም ዐወቁ። |
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ውዷን ተደግፋ፣ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን ወለደችህ።
አንተ ግን እንደማይፈለግ ቅርንጫፍ፣ ከመቃብር ወጥተህ ተጥለሃል፤ በሰይፍ በተወጉት፣ ወደ ጥልቁ ድንጋዮች በወረዱት፣ በተገደሉትም ተሸፍነሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
በመጣህ ጊዜ ሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣ በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤ በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታት ከዙፋናቸው አውርዳለች።
ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።
እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋራ ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”