እንደ ውሻ እያላዘኑ፣ በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤ በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።
አንተም አቤቱ፥ የኃያላን አምላክ፥ የእስራኤል አምላክ፥ አሕዛብን ሁሉ ትጐበኛቸው ዘንድ ተነሥ፥ ክፉ ከዳተኞችን ሁሉ አትማራቸው።
እነርሱ በከተማይቱ ውስጥ እንደ ውሻ እያላዘኑ ሲልከሰከሱ ውለው ወደ ማታ ይመለሳሉ።
እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፤ ደስ ይለኛል፥ ምርኮንም እካፈላለሁ፥ የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ።
አምላኬ ሆይ፤ የክህነትን ማዕርግ፣ የክህነትንና የሌዋውያንን ቃል ኪዳን ስላረከሱ ዐስባቸው።
ውሾች ከበቡኝ፤ የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤ እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።
ሳኦልም የዳዊትን ቤት ከብበው በማለዳ እንዲገድሉት ሰዎችን ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮል ግን፣ “ሕይወትህን ለማትረፍ በዚህች ሌሊት ካልሸሸህ፣ በነገው ቀን ትገደላለህ” ብላ አስጠነቀቀችው።