ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎትና ስለ ምሕረት ያቀረበውን ልመና አድምጥ፤ በዛሬው ዕለት ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ጸሎት ስማ።
መዝሙር 5:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሤና አምላኬ ሆይ፤ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ ድረስልኝ ብዬ ስጮኽ ስማኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ መቃተቴንም አስተውል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሤና አምላኬ ሆይ! ወደ አንተ ስለምጸልይ ለእርዳታ የምጮኸውን ጩኸት አድምጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና። |
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ የባሪያህን ጸሎትና ስለ ምሕረት ያቀረበውን ልመና አድምጥ፤ በዛሬው ዕለት ባሪያህ በፊትህ የሚያቀርበውን ጩኸትና ጸሎት ስማ።
ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።