አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
መዝሙር 26:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱ እጅ የተንኰል ዕቅድ አለ፤ ቀኝ እጃቸውም ጕቦን ያጋብሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም በጉቦ ተሞልታለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ጣቶቻቸው ክፉ ሥራን ለመሥራት የነቁ፥ ቀኝ እጆቻቸውም በጉቦ የተሞሉ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቴና እናቴ ጥለውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ። |
አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? “ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤ የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።
በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣
ኀጢአታችሁ ምንኛ ታላቅ እንደ ሆነ፣ በደላችሁም የቱን ያህል እንደ በዛ እኔ ዐውቃለሁና። ጻድቁን ትጨቍናላችሁ፤ ጕቦም ትቀበላላችሁ፤ በፍርድ አደባባይም ከድኻው ፍትሕ ትነጥቃላችሁ።
እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዥው እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጕቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።