አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር።
ምሳሌ 7:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤ በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፥ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚማርኩ ቃሎችዋ አግባባችው፤ በለዘበ አነጋገርዋም አታለለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ወጥመድም ትጐትተዋለች። |
አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር።
እነርሱ ግን፣ “ምሽት እየተቃረበ፣ ቀኑም እየተገባደደ ስለ ሆነ ከእኛ ጋራ ዕደር” ብለው አጥብቀው ለመኑት፤ ስለዚህ ከእነርሱ ጋራ ለማደር ገባ።
ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የዕንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።
እርሱም፣ “አልበላም” በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትየዋ ጋራ ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ፤ ከመሬትም ተነሥቶ በዐልጋ ላይ ተቀመጠ።