ዘኍል 7:89 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ ከምስክሩ ታቦት መክደኛ በላይ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምፅ ሲናገረው ሰማ፤ አነጋገረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ከጌታ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እንዲህም እርሱ ተናገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በኪሩቤል መካከል ካለው ከቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ በላይ ሆኖ ሲናገረው ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ወደ ምስክሩ ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው በላይ ከኪሩቤልም መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ይናገር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እርሱም ይናገረው ነበር። |
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን በሲና ምድረ በዳ ሳሉ እግዚአብሔር ሙሴን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ተናገረው፤ እንዲህም አለው፤
ወደዚያም ወርጄ አነጋግርሃለሁ፤ ባንተ ላይ ካለው መንፈስ ወስጄ በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ የሕዝቡንም ሸክም ብቻህን እንዳትሸከም እነርሱ ያግዙሃል።
እኔ ከርሱ ጋራ የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤ በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤ እርሱ የእግዚአብሔርን መልክ ያያል። ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴን ትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”
አሁን ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ ወንጌልን ያበሠሩላችሁ ሰዎች የነገሯችሁን ነገር ባወሩላችሁ ጊዜ፣ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው። መላእክትም እንኳ ሳይቀሩ እነዚህን ነገሮች ይመኛሉ።
ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፣ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ጋራ በዚያ ነበሩ።