ይህ የሆነው እስራኤልን በምግብና ውሃ መስተንግዶ በመቀበል ፈንታ፣ በለዓም እንዲረግምላቸው በገንዘብ ስለ ገዙት ነበር። ይሁን እንጂ አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።
ዘኍል 24:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ያዕቆብ ሆይ፤ ድንኳኖችህ፣ እስራኤል ሆይ፤ ማደሪያዎችህ እንዴት ያማሩ ናቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብ ሆይ! ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ! ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ፥ የሰፈርክባቸው ቦታዎች ምንኛ ያምራሉ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብ ሆይ፥ ቤቶችህ፥ እስራኤል ሆይ ድንኳኖችህ ምንኛ ያምራሉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ! |
ይህ የሆነው እስራኤልን በምግብና ውሃ መስተንግዶ በመቀበል ፈንታ፣ በለዓም እንዲረግምላቸው በገንዘብ ስለ ገዙት ነበር። ይሁን እንጂ አምላካችን ርግማኑን ወደ በረከት ለወጠው።
ለማደሪያው ድንኳን፣ ይኸውም ለምስክሩ ድንኳን ሙሴ ባዘዘው፣ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር መሪነት ሌዋውያኑ በጻፉት መሠረት የዕቃዎቹ ቍጥር ይህ ነው።
ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።
“እንደ ሸለቆዎች፣ በወንዝ ዳር እንዳሉም የአትክልት ስፍራዎች ተዘርግተዋል፤ በእግዚአብሔር እንደ ተተከሉ አደሶች፣ በውሃም አጠገብ እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው።
ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።”