ዘኍል 17:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “እነሆ መሞታችን ነው! ጠፋን፤ ሁላችንም መጥፋታችን ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እነሆ፥ እንሞታለን፥ እንጠፋለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “እንዲህ ከሆነማ እኛ ሁላችንም ማለቃችን ነው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ሙሴን አሉት፥ “እነሆ፥ እንሞታለን፤ እንጠፋለን፤ ሁላችንም እናልቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ሙሴን፦ እነሆ፥ እንሞታለን፥ እንጠፋለን፥ ሁላችንም እንጠፋለን። |
እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ።
ልጆች እንደ መሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፤ የጌታን ተግሣጽ አታቃልል፤ በሚቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤