በማግስቱም በእግዚአብሔር ፊት እሳትና ዕጣን ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔር የሚመርጠውም ያ ሰው ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ናችሁ።”
ዘኍል 16:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፤ “እናንተ ሌዋውያን ስሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፦ “እናንተ የሌዊ ልጆች፥ እባካችሁ ስሙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ከቆሬ ጋር መነጋገሩን እንዲህ ሲል ቀጠለ፦ “እናንተ ሌዋውያን አድምጡ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ቆሬን አለው፥ “እናንተ የሌዊ ልጆች፥ ስሙኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ቆሬን አለው፦ እናንተ የሌዊ ልጆች፥ ስሙ፤ |
በማግስቱም በእግዚአብሔር ፊት እሳትና ዕጣን ጨምሩባቸው፤ እግዚአብሔር የሚመርጠውም ያ ሰው ቅዱስ ይሆናል፤ እናንተ የሌዊ ልጆች፤ ከልክ ያለፋችሁትስ እናንተ ናችሁ።”
የእስራኤል አምላክ እናንተን ከቀሩት እስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ መለየቱና በእግዚአብሔር ማደሪያ አገልግሎት እንድትፈጽሙ ወደ ራሱ ማቅረቡ፣ እንድታገለግሏቸውም በማኅበረ ሰቡ ፊት እንድትቆሙ ማድረጉ አይበቃችሁምን?