ዘኍል 12:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ በማኅፀን እንደ ሞተ ልጅ እርሷ እባክህ፥ አትሁን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ እንደ ተወለደ ጭንጋፍ እንድትመስል አታድርግ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናቱ ማኅፀን ሞቶ እንደ ተወለደ፥ ከተበላ ግማሽ ሥጋዋ ጋር ለሞት አትተዋት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናቱ ሆድ በወጣ ጊዜ ግማሽ ሥጋው ተበልቶ እንደ ሞተ እርስዋ አትሁን። |
እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለመገረዝ ሙታን ነበራችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ከክርስቶስ ጋራ ሕያዋን አደረጋችሁ፤ በደላችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤