ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
ዘኍል 1:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ ተቈጥረው የነበሩ ናቸው፤ እነርሱን ሙሴና አሮን ከእስራኤል አለቆች፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ቤቶች ይወክሉ ከነበሩ ጋር በመሆን ቈጠሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ የራሱን ወገን ወክሎ በመምጣት በዐሥራ ሁለቱ የነገድ መሪዎች ርዳታ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው እነዚህ ናቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮን ዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች እነርሱን የቈጠሩበት ቍጥር ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን አሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዱ የአባቶቹ ቤት አለቃ ነበረ። |
ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት በየቤተ ሰባቸው ተቈጠሩ፤