ነህምያ 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ ሁለተኛ አውራጃ የበላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቃቸውም የዚክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፤ የሃስኑአ ልጅ ይሁዳ ደግሞ በከተማው ላይ ሁለተኛ የተሾመ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል መሪያቸው ሲሆን፥ የሀስኑአ ልጅ ይሁዳ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነ የከተማይቱ ባለሥልጣን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሰኑዋም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበር፥ የሐስኑአም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ። |
በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሸብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።