ማቴዎስ 9:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ ቍራጭ ጨርቅ የሚጥፍ ሰው የለም፤ ይህ ከሆነ አዲሱ ዕራፊ ካረጀው ልብስ ላይ ተቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአረጀ ልብስ ላይ አዲስ ዕራፊ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ቢጣፍ ግን አዲሱ ዕራፊ አሮጌውን ልብስ ቦጭቆ ቀዳዳውን የባሰ ያሰፋዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያም ጊዜ ይጾማሉ።
አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ ማንም አያስቀምጥም፤ ይህ ከሆነ አቍማዳው ይፈነዳል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቍማዳውም ከጥቅም ውጭ ይሆናል። ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ አቍማዳ ይጨመራል፤ በዚህ ሁኔታ የወይን ጠጁና አቍማዳው በደኅና ተጠብቀው ይቈያሉ።”
“በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ ቍራጭ ጨርቅ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ይህ ቢደረግ ግን፣ አዲሱ ጨርቅ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፤ ቀዳዳውም የባሰ ይሰፋል።
ደግሞም እንዲህ ሲል ምሳሌ ነገራቸው፤ “ከአዲስ ልብስ ላይ ቍራጭ ጨርቅ ቀድዶ በአሮጌ ልብስ ላይ የሚጥፍ ማንም የለም፤ እንዲህ ቢደረግ አዲሱ ልብስ ይቦጨቃል፤ አዲሱም ዕራፊ ለአሮጌው ልብስ አይስማማውም።