ሉቃስ 23:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ጥያቄዎችንም አቀረበለት፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰለትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብዙ ቃልም ጠየቀው፤ እርሱ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሄሮድስ ኢየሱስን ብዙ ጥያቄ ጠየቀው፤ ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብዙ ነገርም መረመረው፤ እርሱ ግን አንድስ እንኳ አልመለሰለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብዙ ቃልም ጠየቀው፤ እርሱ ግን አንድ ስንኳ አልመለሰለትም። |
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ሄዳችሁ ለዚያ ቀበሮ፣ እነሆ፤ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ ሕመምተኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን ከግቤ እደርሳለሁ ብሏል በሉት፤
ጃንደረባው ያነብብ የነበረው የመጽሐፍ ክፍል ይህ ነበር፤ “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፤ በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ አፉን አልከፈተም።