ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።
ሉቃስ 23:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስም ኢየሱስን ብዙ ጊዜ ሊያየው ይፈልግ ስለ ነበር፣ ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ታምራት ሲሠራ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፤ ተአምር ሲሠራ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄሮድስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ ኢየሱስ ይሰማ ነበርና ሊያየው ብዙ ጊዜ ይመኝ ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄሮድስም ጌታችን ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜናውን ስለሚሰማ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይሻ ነበርና፤ የሚያደርገውንም ተአምራት ሊያይ ይመኝ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፥ ምልክትም ሲያደርግ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር። |
ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።
የኢየሱስ ስም እየታወቀ በመምጣቱ፣ ንጉሥ ሄሮድስ ይህንኑ ሰማ። አንዳንዶችም፣ “የዚህ ዐይነት ታምር በርሱ የሚሠራው መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ቢነሣ ነው” ይሉ ነበር።
ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።
እርሱም፣ “ ‘ባለመድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው።