ሉቃስ 19:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በዚያ በኩል ያልፍ ስለ ነበር ዘኬዎስ እርሱን ለማየት ብሎ ከሕዝቡ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ፊቱም ሮጠ፤ ያየው ዘንድም በሾላ ላይ ወጣ፤ በዚያች መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ። |
ጌድራዊው በአልሐናን በምዕራባዊው ኰረብቶች ግርጌ ለሚገኙት የወይንና የወርካ ዛፎች ጥበቃ ኀላፊ ነበረ፤ በዘይቱም ቤቶች ላይ ኢዮአስ ሹም ነበረ።
ጌታም እንዲህ አላቸው፣ “የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ፣ ይህን ሾላ፣ ‘ተነቅለህ ባሕር ውስጥ ተተከል’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል”።
ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ቤቱ ውስጥ ማስገባት ስላቃታቸው፣ ጣራው ላይ ወጥተው የቤቱን ክዳን በመንደል በሽተኛውን ከነዐልጋው በሕዝቡ መካከል ቀጥታ ኢየሱስ ፊት አወረዱት።