ሉቃስ 19:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችም እርሱ በሚሄድበት መንገድ ላይ ልብሶቻቸውን ያነጥፉ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ሲሄድ ሳለ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሄዱም በመንገድ ልብሳቸውን አነጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። |
በደብረ ዘይት ተራራ ቍልቍል ወደሚወስደው መንገድ በተቃረቡ ጊዜ፣ ቍጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት ስላዩት ታምራት ሁሉ ደስ እያላቸው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲህ እያሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ጀመር፤