ኤርምያስ 6:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የተረፉትን ፈጽሞ ይለቅሙአችኋል፤ እጅህንም እንደ ለቃሚ በቅርንጫፎቹ ላይ ዳግመኛ ዘርጋ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእስራኤል የተረፉትን የወይን ዘለላን እንደሚለቅም ሰው ልቀሙ፤ መላልሳችሁ ወይንን እንደሚለቅም ሰው እጃችሁን በቅርንጫፎቹ ላይ ዘርጉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ወይንን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ይቃርሙአቸዋል፤ እጅህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰው ወይኑን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ፈጽሞ ይቃርሙአቸዋል፥ እጅህንም እንደ ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ። |
“አሁን ግን ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እነርሱም ያጠምዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ ዐዳኞችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ከየተራራው፣ ከየኰረብታው ሁሉ ከየዐለቱም ስንጣቂ ዐድነው ይይዟቸዋል።
በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ የያዘውን፣ “ዘለላው ስለ በሰለ፣ ስለታም ማጭድህን ያዝና በምድር ላይ ያሉትን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።