ኤርምያስ 51:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ጦረኞች መዋጋት ትተዋል፤ በምሽጎቻቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸው ተሟጥጧል፤ እንደ ሴት ሆነዋል፤ በማደሪያዎቿም እሳት ተለኵሷል፤ የደጇም መወርወሪያ ተሰብሯል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፥ ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፥ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። |
እነሆ፣ እነርሱ ገለባ ናቸው፤ እሳት ይበላቸዋል፤ ከነበልባሉ ወላፈን የተነሣ፣ ራሳቸውን ማዳን አይችሉም። ሰው የሚሞቀው ፍም አይኖርም፤ ተቀምጠው የሚሞቁትም እሳት የለም።
ከየአቅጣጫው ጩኹባት፤ እጇን ትሰጣለች፤ ምሽጓም ይወድቃል፤ ቅጥሮቿ ይፈርሳሉ። ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና፣ እርሷን ተበቀሏት፤ በሌሎቹ ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።
ባለሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።
በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤ የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤ ንጉሧና መሳፍንቷ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰድደዋል፤ ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤ ነቢያቷም ከእንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም።
የደማስቆን በሮች እሰባብራለሁ፤ በቤት ዔደን በትር የያዘውን፣ በአዌን ሸለቆ ያለውን ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርኮ ወደ ቂር ይሄዳል” ይላል እግዚአብሔር።
ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው እንዲህ ይላሉ፤ “ ‘አንቺ ታላቂቱ ከተማ ወዮልሽ! ወዮልሽ! አንቺ ባቢሎን ብርቱዪቱ ከተማ፣ ፍርድሽ በአንድ ሰዓት ውስጥ መጥቷል።’