የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
ኤርምያስ 47:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖን ጋዛን ድል ከማድረጉ በፊት፣ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ጋዛን ከመምታቱ በፊት ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ንጉሥ በጋዛ ላይ አደጋ ከመጣሉ በፊት እግዚአብሔር ስለ ፍልስጥኤም እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ጋዛን ሳይመታ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ጋዛን ሳይመታ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። |
የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ስቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።
በዚያ የሚኖሩትን ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታትን ሁሉ፣ በአስቀሎና፣ በጋዛ፣ በአቃሮንና በአዛጦንም ሕዝብ ቅሬታ ያሉትን የፍልስጥኤም ነገሥታት፣
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ፍልስጥኤማውያን በቂም ተነሣሥተው በክፉ ልብ ተበቅለዋልና፣ ይሁዳንም በቈየ ጠላትነት ለማጥፋት ፈልገዋልና፤
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ክንዴን በፍልስጥኤማውያን ላይ አነሣለሁ፤ ከሊታውያንንም እቈርጣለሁ፤ በባሕሩ ጠረፍ ላይ የቀሩትንም አጠፋለሁ።
“ጢሮስና ሲዶና እንዲሁም እናንተ የፍልስጥኤም ግዛቶች ሁሉ ሆይ፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ምን አላችሁ? ስላደረግሁት ነገር ብድር ልትመልሱልኝ ነውን? የምትመልሱልኝ ከሆነ፣ በፍጥነትና በችኰላ እናንተ ያደረጋችሁትን በራሳችሁ ላይ መልሼ አደርግባችኋለሁ።