ኤርምያስ 12:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ ባድማ፣ ደረቅና ወና ይሆናል፤ መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት ማንም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድረ በዳም ስላደረጉአት በፊቴ ባድማ ሆናለች፤ አገሪቱ በሙሉ ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ስለ እርስዋም የሚገደው አንድ እንኳ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ለፍጹም ጥፋት ሆናለች፤ ስለ እኔም ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች፤ በልቡም የሚያኖራት የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፥ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም። |
ስለዚህ የሚነድድ ቍጣውን፣ የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤ በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።
ጻድቅ ይሞታል፤ ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣ መወሰዳቸውን፣ ማንም አያስተውልም።
ያዕቆብን አሟጥጠው ስለ በሉት፣ ፈጽመው ስለ ዋጡት፣ መኖሪያውንም ወና ስላደረጉ፣ በማያውቁህ ሕዝቦች፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ፣ ቍጣህን አፍስስ።
ይህችን ከተማ ድምጥማጧን አጠፋለሁ፤ የድንጋጤና መሣለቂያም ምልክት አደርጋታለሁ፤ በዚያም የሚያልፉ ሁሉ ከቍስሎቿም የተነሣ ወይ ጉድ! ይላሉ፣ ያሾፋሉም።
ምድሪቱ በአመንዝሮች ተሞልታለች፤ ከርግማን የተነሣ ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ በምድረ በዳ ያሉት መሰማሪያዎች ደርቀዋል። ነቢያቱም ጠማማ መንገድ ተከትለዋል፤ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ ተጠቅመዋል።
ስለ ተራሮች አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይ እላለሁ፤ በምድረ በዳ ስላሉትም መሰማሪያዎች ዐዝናለሁ። ሰው የማያልፍባቸው ባድማ ሆነዋል፤ የከብቶች ጩኸት አይሰማም፤ የሰማይ ወፎች ሸሽተዋል፤ የዱር አራዊትም ጠፍተዋል።
“የምድሩን ሕዝብ ሁሉና ካህናቱን እንዲህ በላቸው፤ ‘ባለፉት ሰባ ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት በርግጥ ለእኔ ነበርን?
ባትሰሙ፣ ልባችሁንም ስሜን ለማክበር ባታዘጋጁ፣ ርግማን እሰድድባችኋለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ መርገም እለውጠዋለሁ፤ ልታከብሩኝ ልባችሁን አላዘጋጃችሁምና ረግሜዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።