እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣ “ዛፉን ከፍሬው ጋራ እንቍረጥ፤ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ” ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።
ኤርምያስ 11:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚቀጡበት ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ መዓት ስለማመጣ፣ ከእነርሱ የሚተርፍ አንድም አይኖርም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚተርፍ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐናቶት ሕዝብ ላይ መቅሠፍት የማመጣበት ዘመን ሲደርስ ከእነርሱ መካከል አንድ ሰው እንኳ አይተርፍም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚተርፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምጐበኛቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም። |
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣ “ዛፉን ከፍሬው ጋራ እንቍረጥ፤ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ” ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።
“ስለዚህ መንገዳቸው ድጥ ይሆናል፤ ወደ ጨለማ ይጣላሉ፤ ተፍገምግመውም ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ዓመት፣ መዓት አመጣባቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ቅጥረኞች ወታደሮቿም እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣ እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤ በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።
“ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ ጕድጓድ ውስጥ ይገባል፤ ከጕድጓዱም የሚወጣ፣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ፣ የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣” ይላል እግዚአብሔር።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”
ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
የቅጣት ቀን መጥቷል፤ የፍርድም ቀን ቀርቧል፤ እስራኤልም ይህን ይወቅ! ኀጢአታችሁ ብዙ፣ ጠላትነታችሁም ታላቅ ስለ ሆነ፣ ነቢዩ እንደ ቂል፣ መንፈሳዊውም ሰው እንደ እብድ ተቈጥሯል።
የያዕቆብ ቤት እሳት፣ የዮሴፍም ቤት ነበልባል ይሆናል፤ የዔሳው ቤት ገለባ ይሆናል፤ ያቃጥሉታል፤ ይበሉትማል፤ ከዔሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም።” እግዚአብሔር ተናግሯል።
ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜከላ፣ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኵርንችት ነው፤ የጠባቂዎቻችሁ ቀን ደርሷል፤ የአምላክ የፍርድ ቀን መጥቷል፤ የሚሸበሩበትም ጊዜ አሁን ደርሷል።