እኔም እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላቸዋለሁ፤ ስለ ስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስም እተወዋለሁ፤ ከዚያም እስራኤል በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ይሆናሉ፤
ሆሴዕ 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ምድር አይቀመጡም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፤ የረከሰውንም ምግብ በአሦር ይበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኩስን ነገር ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር አይኖሩም፤ ነገር ግን ተገደው ወደ ግብጽ ይመለሳሉ፤ ወደ አሦርም ሄደው በሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ምግብ ይበላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም በግብፅ ይቀመጣል፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይቀመጡም፥ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኵስን ነገር ይበላሉ። |
እኔም እስራኤልን ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላቸዋለሁ፤ ስለ ስሜ የቀደስሁትን ይህን ቤተ መቅደስም እተወዋለሁ፤ ከዚያም እስራኤል በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ መተረቻና መዘባበቻ ይሆናሉ፤
በሆሴዕ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም በምርኮ ወደ አሦር አፈለሳቸው። እነዚህም በአላሔ፣ ጎዛን ውስጥ በአቦር ወንዝ አጠገብ እንዲሁም በማዴ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለ ሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው፤ መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ በዚህም ምክንያት በግብጽ ምድር፣ መዘባበቻ ይሆናሉ።”
ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
ከጥፋት ቢያመልጡም እንኳ፣ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ሀብታቸውን ዳዋ ያለብሰዋል፤ ድንኳኖቻቸውንም እሾኽ ይወርሳቸዋል።
“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ሚስትህ በከተማዪቱ ውስጥ ጋለሞታ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ እየተለካ ይከፋፈላል፤ አንተ ራስህ በረከሰ ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከትውልድ አገሩ፣ ተማርኮ ይሄዳል።’ ”
እግዚአብሔር እናንተን በማበልጸግና ቍጥራችሁን በማብዛት ደስ እንደ ተሠኘ፣ እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስም ደስ ይለዋል፤ ልትወርሷት ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ።
ዳግመኛ አትመለስባትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብጽ ይመልስሃል። እዚያም ወንዶችና ሴቶች ባሮች እንድትሆኗቸው ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ፤ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።
ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ላይ ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክሮች አድርጌ እጠራለሁ፤ በዚያ ቦታ ብዙ ዘመን አትኖሩም፤ ፈጽሞ ትጠፋላችሁ።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁ መልካሙ ተስፋ በሙሉ እንደ ተፈጸመ ሁሉ፣ እንደዚሁም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር እስኪያጠፋችሁ ድረስ ክፉውን ነገር ያመጣባችኋል።