ዘፍጥረት 7:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነም እንስሳ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ |
ከዚያም ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ መሠዊያው ላይ ንጹሕ ከሆኑት እንስሳት ሁሉ፣ እንዲሁም ንጹሕ ከሆኑት ወፎች የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤