ዘፍጥረት 30:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ወንድ ልጅ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላም ፀነሰችና ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የራሔል አገልጋይ ባላም ፀነስች፤ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። |
እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
ከዳን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ።