ዘፍጥረት 24:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ” የምትለኝ እርሷ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ የመረጣት ትሁን።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ የምትለኝ፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ያዘጋጃት ሴት እርሷ ትሁን።’” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ‘እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳላቸዋለሁ’ የምትለኝ ብትሆን፥ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥካት እርስዋ ትሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ለባሪያዉ ለይስሐቅ ያዘጋጃት ሚስት እርስዋ ትሁን። በዚህም ለጌታዬ ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አንተ ጠጣ ደግሞም ለግመሎችህ እቀዳለሁ የምትለኝ እግዚአብሔር ለጌታዬ ልጅ ያዘጋጃት ሴት እርስዋ ትሁን። |
እንግዲህ፣ ‘እንስራሽን አውርጂና ውሃ አጠጪኝ’ ስላት፣ ‘ዕንካ ጠጣ፤ ግመሎችህንም ላጠጣልህ’ የምትለኝ ቈንጆ እርሷ ለባሪያህ ለይሥሐቅ የመረጥሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ቸርነትህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።”
“በልቤ የምጸልየውን ጸሎት ገና ሳልጨርስ፣ ርብቃ እንስራዋን በትከሻዋ ላይ አድርጋ ብቅ አለች፤ ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ ቀዳች። እኔም፣ ‘እባክሽ፤ ውሃ አጠጪኝ’ አልኋት።