ዘዳግም 4:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ በእስራኤላውያን ፊት የደነገገው ሕግ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ ለእስራኤላውያን ያቀረበው ሕግ ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት፤ |
ከኢያሪኮ ማዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ ሳሉ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዞችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።
የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፣ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው።
ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።
እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤