ከዚያም ኢዩ፣ “እንግዲህ የእኔ ወገን ከሆናችሁና ከታዘዛችሁኝ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቈርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ይዛችሁልኝ ወደ ኢይዝራኤል እንድትመጡ” ሲል ደግሞ ጻፈላቸው። በዚህም ጊዜ ሰባው የንጉሡ ልጆች በከተማዪቱ ውስጥ ታዋቂ በሆኑ አሳዳጊዎቻቸው ዘንድ ነበሩ።
2 ነገሥት 10:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ኢዩ ወጥቶ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በመቆም እንዲህ አለ፤ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ ጌታዬን ያሤርሁበትና የገደልሁት እኔ ነኝ። እነዚህን ሁሉ ግን የፈጃቸው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ማለዳ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር ሄዶ በዚያ ለተሰበሰቡት ሕዝብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “በንጉሥ ኢዮራም ላይ በማሤር የገደልኩት እኔ ነበርኩ፤ ስለዚህም እናንተ በዚያ ጉዳይ አትጠየቁበትም፤ ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የገደለ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ማለዳ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር ሄዶ በዚያ ለተሰበሰቡት ሕዝብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “በንጉሥ ኢዮራም ላይ በማሤር የገደልኩት እኔ ነበርኩ፤ ስለዚህም እናንተ በዚያ ጉዳይ አትጠየቁበትም፤ ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የገደለ ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ፥ “እናንተ ንጹሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌታዬን ቤት የወነጀልሁ የገደልኋቸውም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝቡንም ሁሉ “እናንተ ንጹሐን ናችሁ፤ እነሆ፥ ጌታዬን የወነጀልሁ የገደልሁትም እኔ ነኝ፤ እነዚህንስ ሁሉ የገደለ ማን ነው? |
ከዚያም ኢዩ፣ “እንግዲህ የእኔ ወገን ከሆናችሁና ከታዘዛችሁኝ የጌታችሁን ልጆች ራስ ቈርጣችሁ ነገ በዚህ ሰዓት ይዛችሁልኝ ወደ ኢይዝራኤል እንድትመጡ” ሲል ደግሞ ጻፈላቸው። በዚህም ጊዜ ሰባው የንጉሡ ልጆች በከተማዪቱ ውስጥ ታዋቂ በሆኑ አሳዳጊዎቻቸው ዘንድ ነበሩ።
መልእክተኛው እንደ ደረሰም፣ ለኢዩ፣ “የንጉሡን ልጆች ራስ አምጥተዋል” ብሎ ነገረው። ከዚያም ኢዩ፣ “በከተማዪቱ መግቢያ በር ላይ ሁለት ቦታ ከምራችሁ እስከ ነገ ጧት ድረስ አቈዩአቸው” ብሎ አዘዘ።
ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “በኢይዝራኤል ስለ ተፈጸመው ግድያ የኢዩን ቤት በቅርቡ ስለምቀጣና የእስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም ስለማደርግ፣ ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጕቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”