1 ሳሙኤል 12:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሳሙኤል ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አለ፤ “ጥያቄአችሁን ሁሉ ተቀብዬ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ አለ፥ “የነገራችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም እስራኤልን ሁሉ አለ፦ የነገራችሁኝን ሁሉ ሰምቼ አንግሼላችኋለሁ። |
ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ብርሌ ወስዶ፣ ዘይቱን በሳኦል ራስ ላይ ካፈሰሰ በኋላ እንዲህ ሲል ሳመው፤ “በርስቱ ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶህ የለምን?
ሳሙኤልም መላውን ሕዝብ፣ “እግዚአብሔር የመረጠውን ሰው አያችሁን? ከሕዝቡ ሁሉ የሚስተካከለው ማንም የለም” አለ። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ብሎ ጮኸ።