Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 11:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በእግዚአብሔር ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ ታላቅ በዓል አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደ፤ የሳኦልንም ንጉሥነት በጌታ ፊት አጸና። በዚያም ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ፤ ሳኦልና እስራኤላውያንም ሁሉ በታላቅ ደስታ አከበሩት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ጌል​ገላ ሄዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ቀብቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ አነ​ገ​ሠው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህል ቍር​ባ​ንና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፥ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፥ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 11:15
12 Referencias Cruzadas  

“ከፊቴ ቀድመህ ወደ ጌልገላ ውረድ፤ እኔም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕቱን ለማቅረብ ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ነገር ግን ወደ አንተ መጥቼ ምን ማድረግ እንዳለብህ እስክነግርህ ድረስ ሰባት ቀን መቈየት አለብህ።”


ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምጽጳ ወደ እግዚአብሔር ፊት ጠርቶ፣


አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲህ ያለው ትምክሕት ሁሉ ክፉ ነው።


አሁን የስንዴ መከር ጊዜ አይደለምን? እኔ ነጐድጓድና ዝናብ እንዲልክ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እናንተም ንጉሥ እንዲነግሥላችሁ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት የቱን ያህል የከፋ ድርጊት እንደፈጸማችሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ።”


ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እንቢ በማለት፤ እንዲህ አሉ፤ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን፤


ከዚያም ወጣት ወንድ እስራኤላውያንን ላከ፤ እነርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ወይፈኖችን የኅብረት መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር ሠዉ።


ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።


ከዚያም ንጉሡ ተመልሶ እስከ ዮርዳኖስ ድረስ መጣ። በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን ተቀብለው ዮርዳኖስን ለማሻገር እስከ ጌልገላ ድረስ መጥተው ነበር።


ሳሙኤልም መላውን ሕዝብ፣ “እግዚአብሔር የመረጠውን ሰው አያችሁን? ከሕዝቡ ሁሉ የሚስተካከለው ማንም የለም” አለ። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር!” ብሎ ጮኸ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios