ሩት 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ሕይወትሽን ያድሳታል፤ በእርጅና ዘመንሽም ይጦርሻል፤ የምትወድድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ ወልዳዋለችና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፤ በእርጅናሽም ይመገባሻል፤” አሉአት። |
አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።
ከዚህም የተነሣ ባልዋ ሕልቃና “ሐና ሆይ! ስለምን ታለቅሻለሽ? ስለምንስ አትመገቢም? ስለምንስ ዘወትር ይህን ያኽል ታዝኚአለሽ? ከዐሥር ልጆች ይልቅ እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።
ጠግበው የነበሩ ተርበው ለምግብ ተገዝተዋል፤ ተርበው የነበሩ ግን ጠግበዋል፤ መኻኒቱ ሰባት ወለደች፤ የብዙዎች ልጆች እናት የነበረችው ብቻዋን ቀረች።