ቦዔዝም “ሸማሽን ከላይሽ አንሺና ወደዚህ ዘርጊው” አላት። እርስዋም ሸማዋን ዘረጋች፤ ቦዔዝም ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፈረላትና አንሥቶ በትከሻዋ አሸከማት። ከዚያም እርሱ ወደ ከተማ ሄደ።
ሩት 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዐማትዋም በመጣች ጊዜ ዐማትዋ “ልጄ ሆይ! ያ ጉዳይ እንዴት ሆነልሽ?” አለቻት። ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሩት ወደ ዐማቷ እንደ ተመለሰች፣ ኑኃሚን፣ “ልጄ ሆይ፤ የሄድሽበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” ብላ ጠየቀቻት። ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አማትዋም በመጣች ጊዜ አማቷ፦ “ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ?” አለቻት፥ እርሷም ሰውየው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። ወደ አማትዋም መጣች፥ አማትዋም፦ ልጄ ሆይ እንዴት ነሽ? አለቻት፣ እርስዋም ሰውዮው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ወደ ከተማይቱ ሄደ። ወደ አማትዋም መጣች፤ አማትዋም “ልጄ ሆይ! እንዴት ነሽ?” አለቻት፤ እርስዋም ስውዮው ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት። |
ቦዔዝም “ሸማሽን ከላይሽ አንሺና ወደዚህ ዘርጊው” አላት። እርስዋም ሸማዋን ዘረጋች፤ ቦዔዝም ወደ ኻያ ኪሎ የሚጠጋ ገብስ ሰፈረላትና አንሥቶ በትከሻዋ አሸከማት። ከዚያም እርሱ ወደ ከተማ ሄደ።