ሮሜ 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኛ አይሁድ ከአሕዛብ እንበልጣለን ማለት ነውን? ከቶ አይደለም! ሰዎች ሁሉ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ቀደም ብዬ አስረድቻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ምን እንላለን? እኛ ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፤ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ፣ ሁሉም ከኀጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከስሰናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ምን ይሁን? እኛ እንበልጣለንን? በጭራሽ! አይሁዳውያንንም ግሪካውያንንም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ምን እንላለን? ከእነርሱ እንበልጣለን? አይደለም፤ አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥ አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ ሁሉም ስተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምን ይሁን? ከእነርሱ እንበልጣለንን? ከቶ አይደለም፤ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና፤ |
እነርሱ፥ ‘እኛ ቅዱሳን ስለ ሆንን ወደ እኛ አትቅረቡ!’ የሚሉ ናቸው፤ እነዚህ ነገሮች ቀኑን ሙሉ ለሚነድ እሳት ኀይለኛ ቊጣዬን የሚያቀጣጥሉ ናቸው።
ምሳ የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህን ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነችና ምን ዐይነት ኃጢአተኛ እንደ ሆነች ባወቀ ነበር፤” ሲል በልቡ አሰበ።
ሰዎች በክፋታቸው እውነት እንዳይታወቅ ያደርጋሉ፤ እግዚአብሔርንም ባለመፍራታቸውና በክፋታቸው ምክንያት በሁሉም ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ከሰማይ ይገለጣል።
በሌላው ሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ለራስህ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ሰው ላይ ስትፈርድ በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ አንተ በሰው ላይ እየፈረድክ፥ ያ የፈረድክበት ሰው የሚያደርገውን ታደርጋለህ።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
ነገር ግን የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ቢቀጣን ትክክለኛ ፈራጅ አይደለም ማለት ነውን? እዚህ ላይ የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።
ታዲያ፥ ምን ማድረግ ይገባኛል? በመንፈሴ እጸልያለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እጸልያለሁ፤ በመንፈሴ እዘምራለሁ፤ በአእምሮዬም ደግሞ እዘምራለሁ።
አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?
“በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ትእዛዞች ሁሉ ጸንቶ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ “ሕግን በመፈጸም እንጸድቃለን” የሚሉ ሁሉ የተረገሙ ናቸው።
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።