የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ፥ ዖዴድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በሰማርያ ከተማ ይኖር ነበር፤ የእስራኤል ሠራዊት አይሁድን እስረኞች አድርገው በመውሰድ ወደ ሰማርያ ከተማ በመግባት ላይ ሳሉ ወደ እነርሱ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ ስለ ተቈጣ እነርሱን ድል እንድታደርጉአቸው አደረገ፤ እናንተ ግን ወደ ሰማይ በደረሰ ቊጣ ፈጃችኋቸው፤
ራእይ 18:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኃጢአትዋ ክምር እስከ ሰማይ ደርሶአል፤ እግዚአብሔር በደሎችዋን አስታውሶአል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተከምሯልና፤ እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አስታውሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፤ እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አስታወሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፤ እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ። |
የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ፥ ዖዴድ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው በሰማርያ ከተማ ይኖር ነበር፤ የእስራኤል ሠራዊት አይሁድን እስረኞች አድርገው በመውሰድ ወደ ሰማርያ ከተማ በመግባት ላይ ሳሉ ወደ እነርሱ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ ስለ ተቈጣ እነርሱን ድል እንድታደርጉአቸው አደረገ፤ እናንተ ግን ወደ ሰማይ በደረሰ ቊጣ ፈጃችኋቸው፤
“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
በዚያ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲህ አሉ፦ ‘ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፤ እርሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም፤ የተፈረደባት ፍርድ እስከ ደመና ድረስ ከፍ ስላለና ከዚያም በላይ እስከ ሰማይ ድረስ ስለ ደረሰ ትተናት እያንዳንዳችን ወደየሀገራችን እንሂድ።’ ”
“ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።”
ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።