ራእይ 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ያየኸውን፥ አሁን ያለውንና በኋላ የሚመጣውን ጻፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ ያየኸውን፣ አሁን ያለውንና በኋላም የሚሆነውን ጻፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ የሚሆነውን ጻፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ። |
ይህ ራእይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ይህን ራእይ ገለጠለት።
“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”
ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ እኔ ልጽፍ አሰብኩ፤ ነገር ግን “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን አሽገህ በምሥጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው!” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።
ከዚህ በኋላ መልአኩ “ወደ በጉ ሠርግ ግብዣ የተጠሩ የተባረኩ ናቸው” ብለህ ጻፍ አለኝ፤ ቀጥሎም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው” አለ።