መዝሙር 94:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ሁሉ እያደረጉ “እግዚአብሔር አያየንም፤ የእስራኤል አምላክ አይመለከተንም” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም “እግዚአብሔር አያይም፤ የያዕቆብም አምላክ አያስተውልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ ግን ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። |
ዕቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ወደ ጥልቅ ቦታ ለሚሄዱ በጨለማ የሠሩትንም ሥራ “ማን ያይብናል? ማን ያውቅብናል?” ለሚሉ ሰዎች ወዮላቸው!
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ።
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤
“በዚያን ቀን መብራት ይዤ ኢየሩሳሌምን እፈትሻለሁ፤ በመንደላቀቅ ኑሮ በአተላ ውስጥ አቅርሮ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትንና ‘እግዚአብሔር በጎም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን እቀጣለሁ።