መዝሙር 68:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የባሳን ተራራ ብዙ ወጣ ገባ የሆነና ግርማ ያለው ተራራ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ብርቱ ተራራ፣ የባሳን ተራራ ሆይ፤ አንተ ባለብዙ ጫፍ ተራራ፣ የባሳን ተራራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያዊ ንጉሥ በላይዋ ባዘዘ ጊዜ፥ በሰልሞን ላይ በረዶ ዘነበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የውኃ ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጕድጓዶችም አፋቸውን በኔ ላይ አይክፈቱ፤ |
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።
በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ የዖግ ግዛቶች የሆኑትን በደጋ የሚገኙትን ሳለካና ኤድረዒ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና እንዲሁም የገለዓድንና የባሳንን አውራጃዎች ሁሉ ያዝን።
ስለዚህም ከተከታዮቹ ጋር ወደ ጻልሞን ተራራ ወጣ፤ ከዚያም መጥረቢያ ወስዶ ከዛፍ ላይ እንጨት በመቊረጥ በትከሻው ተሸከመ፤ ተከታዮቹም በፍጥነት እርሱ እንዳደረገው ያደርጉ ዘንድ ነገራቸው።