ሁለንተናውን በጨለማ ሸፈነ፤ በውሃ የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ከቦታል።
ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤ በዝናብ ዐዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።
በኪሩቤልም ሠረገላ ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ አንዣበበ።
ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም ብዙ ዋጋ ይቀበላል።
በጠፈር ላይ ካለው ውሃ በላይ ቤትህን ሠርተሃል፤ ደመና ሠረገላህ ነው፤ በነፋስ ክንፎችም ትሄዳለህ።
በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።
በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤ በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ።
መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥
ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ክብር ከቤተ መቅደሱ መድረክ ተነሥቶ ከኪሩቤል በላይ ወዳለው ስፍራ ወጥቶ ቆመ።
ያ ቀን የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ የጧት ፀሐይ ወገግታ በተራሮች ላይ እንደሚያንሰራፋ፥ ታላቅና ኀያል የአንበጣ መንጋ በየቦታው ይንሰራፋል። ይህን የሚመስል ነገር ከዚህ በፊት አልታየም፤ ከእንግዲህ ወዲህም ምን ጊዜም ቢሆን አይታይም።
“እስከ ሰማይ በሚደርስ የእሳት ነበልባልና ጥቅጥቅ ባለ የጢስ ደመና ወደተጋረደው ተራራ ግርጌ ቀርባችሁ ቆማችሁ።