አንተ ቸር ስለ ሆንክ ቸር የሆነውን ታደርጋለህ፤ ሕጎችህን አስተምረኝ።
አንተ መልካም ነህ፤ የምታደርገው መልካም ነው፤ እንግዲህ ሥርዐትህን አስተምረኝ።
አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥ በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ቸር ስለ ሆነና ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ!
እግዚአብሔር ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ የአንተን ሕግ አስተምረኝ።
አድራጎቴን ሁሉ ተናዘዝኩ፤ አንተም ሰማኸኝ፤ እንግዲህ ሕግህን አስተምረኝ።
ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ።
ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።
ኢየሱስም “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ግን ትእዛዞችን ፈጽም” አለው።
ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ስለምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም ቸር የለም፤
ኢየሱስም “ለምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ማንም ቸር የለም።