ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
መዝሙር 119:49 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ የማደርገው በእርሱ ላይ ስለ ሆነ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃል አስብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ዐስብ፤ በዚያ ተስፋ ሰጥተኸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለባርያህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃልህን አስብ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር።
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ።
ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”
“አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ለዘለዓለም ፈጽም፤ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆን ዘንድ የተናገርከውን ፈጽም፤ ሰዎችም ልዑል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው ይላሉ። የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።
እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ በኢየሱስ አማካይነት እርሱን ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ትተማመናላችሁ።