የሕይወቴ ዘመን እንደ ማታ ጥላ ሆኖአል፤ እንደ ሣርም እጠወልጋለሁ።
ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጸና።
እንደ አበባ ታይቶ ወዲያውኑ ይረግፋል፤ እንደ ጥላም ብዙ ሳይቈይ ወዲያው ያልፋል።
ሰውነቴን በየአቅጣጫው በመቀጥቀጥ ጨርሶ አፈራረሰው፤ የነበረኝንም ተስፋ ሥሩ ተነቃቅሎ እንደሚወድቅ ዛፍ አደረገው።
እንደ ማታ ጥላ ላልፍ ተቃርቤአለሁ፤ እንደ አንበጣም በነፋስ ተወስጄአለሁ።
ሰው እንደ ነፋስ ሽውታ ነው፤ ዘመኑም እንደ ጥላ የሚያልፍ ነው።
ከንቱ ሆኖ እንደ ጥላ በሚያልፍ ዘመኑ ለሰው የሚበጀውን ነገር የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ከሞተ በኋላ በዚህ ዓለም ምን እንደሚሆን ለሰው ማን ሊነግረው ይችላል?
በአምላክ የቊጣ በትር መከራን ያየሁ እኔ ነኝ።
የሰው ሀብት እንደ ሣር አበባ ስለሚረግፍ በኑሮው ከፍ ያለ ወንድም እግዚአብሔር በኑሮው ዝቅ ቢያደርገውም ደስ ይበለው፤
ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ።
መጽሐፍ እንደሚለው፦ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ዱር አበባ ነው፤ ሣሩም ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤