ምሳሌ 5:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ሕይወት በሚመራው መንገድ አትሄድም፤ እንዲሁ ትባዝናለች፤ መባዘንዋን ግን አታውቀውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤ መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለርሷ ግን አይታወቃትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወት መንገድም አትሄድም። መሮጫዋ ሰንከልካላ ነው፥ የሚታወቅም አይደለም። |
ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው።