ምሳሌ 3:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው የተባረከ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዕ ነው፤ ጥበብን የሚያገኛት፣ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርጋት ሰው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥበብን የሚያገኝ ሰው ብጹዕ ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ ሰው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብን የሚያገኝ፥ ማስተዋልንም የሚያውቅ መዋቲ ሰው ብፁዕ ነው። |
‘እርሱን ሰምተን እንታዘዘው ዘንድ ከባሕር ማዶ ተሻግሮ ማን ሊያመጣልን ይችላል?’ ብለህ እንዳትጠይቅ፥ እርሱ የሚገኘው ከባሕር ማዶ አይደለም።