በጎችህ ለልብስ የሚሆን ጠጒር ይሰጡሃል፤ ከፍየሎችህ ጥቂቶቹን በመሸጥ የመሬት መግዣ ገንዘብ ታገኛለህ።
ከበግ ጠቦቶች ልብስ ታገኛለህ፤ ፍየሎችም የዕርሻ መሬት መግዣ ይሆኑሃል።
በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ።
ከበጎቼ ጠጒር የተሠራ ልብስ አልብሼው ሞቆት ሳይመርቀኝ የቀረበት ጊዜ የለም።
ደረቅ ሣር ታጭዶ አዲስ ሣር ሲበቅል፥ በተራራ ላይ ያለው ሣርም ሲሰበሰብ፥
የቀሩት ፍየሎች ለአንተና ለቤተሰብህ ለሴት አገልጋዮችህም ጭምር የሚጠቅም ወተት ይሰጡሃል።
ዐረቦችና የቄዳር ምድር አለቆች ሁሉ ስለ ንግድ ዕቃሽ ጠቦቶች፥ በጎችና ፍየሎች ያመጡልሽ ነበር፤