ምሳሌ 25:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ብትፈጽም በኀፍረት እሳት እንዲቃጠል ታደርገዋለህ፤ ለአንተ ግን እግዚአብሔር የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን በማድረግህም፣ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህ፤ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና፥ ጌታም ይሸልምሃልና። |
ከዚያም በኋላ እነዚያ አራት ሰዎች ለእስረኞቹ ከምርኮው አስፈላጊውን ነገር ሁሉ እንዲሰጡ ተመደቡ፤ እነርሱም ራቊታቸውን ለቀሩት እስረኞች ልብስና ጫማ፥ እንዲሁም በቂ ምግብና ውሃ ሰጡአቸው፤ በቊስላቸውም ላይ የወይራ ዘይት በማፍሰስ ርዳታ አደረጉላቸው፤ በእግር ለመሄድ የማይችሉትን ደካሞችንም በአህያ ላይ አስቀመጡአቸው፤ እስረኞቹም ሁሉ በይሁዳ ግዛት ወደምትገኘው፥ የዘንባባ ዛፍ በብዛት ወደሚገኝባት ወደ ኢያሪኮ ከተማ መልሰው ወሰዱአቸው፤ ከዚህም በኋላ እስራኤላውያን ወደ መኖሪያ ከተማቸው ወደ ሰማርያ ተመለሱ።
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።